በኢትዮጵያ እና በሩዋንዳ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል እና የሩዋንዳ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል በወንጀል የተገኘን ሃብት ህጋዊ ማስመሰል፣ ሽብርተኝነት በገንዘብ መርዳት እና የጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ብዜትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀሎችን በመከላከልና መቆጣጠር ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
የሁለቱ ሀገራት የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከላት በየሀገራቸው ህግ መሰረት በወንጀል ድርጊት የተገኘን ሃብት ህጋዊ አስመስሎ መጠቀም፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት እና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች ብዜትን በገንዘብ መርዳት ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ወንጀሎቹ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የመተንተን እና የማሰራጨት ሀላፊነት ያላቸው ተቋማት ናቸው፡፡
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ሃብት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትንና የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች ብዜትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት በወንጀል ድርጊቶቹ እና ወንጀለኞቹ ዙሪያ መረጃ መለዋወጥና በትብብር መስራት ላይ ያተኮረ ነው።
0 Comments