ባንኮች ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሌሎች የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከል ከፍተኛ ሚና አላቸው
ባንኮች ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ። የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሌሎች የፋይናንስ ወንጀሎች ለመከላከል የባንኮች ሚና በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሐምሌ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ከባንኮች ፕሬዚዳንቶችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ የውይይት መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት አገራችን ወደተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በገባችበት ማግስት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ሌሎች የፋይናንስ ወንጀሎች ለመከላከል የባንኮች ሚናን በተመለከተ እና ሌሎች ማሻሻያውን ተከትሎ መከናወን ስለሚገባቸው የጋራ አገራዊ ጉዳዮቻችን ላይ ለመወያየት መድረኩን መዘጋጀቱን ገልጸው በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው አምስት ቁልፍ ዓላማዎች እና ግቦች በግልጽ መቀመጣቸውን ጠቅሰዋል።
የውጭ ምንዛሪ መዛባትን ማስተካከል እና የረጅም ጊዜ ክፍያ ሚዛን ጉድለት ችግሮችን መፍታት፣ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍን በማዘመን የዋጋ ንረትን መቀነስ፣ የዕዳ ተጋላጭነትን በመፍታት እና የሀገር ውስጥ ገቢን በማሳደግ ሀገራዊ የልማት ፍላጎቶቻችንን በሀገር ውስጥ ዐቅም ለማሳካት ምቹ መደላድል መፍጠር፣ የፋይናንስ ዘርፉን አካታችነት፣ ተወዳዳሪነትና ጤናማነት ማጠናከር፣ እና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም እና የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ፣ ጠንካራ፣ አካታች እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ስርዓትን መገንባት በሚል የተቀመጡ የፖሊሲው ግቦችና ዓላማዎች እንዲሳኩ የሚጠበቅብን አገራዊ ኃላፊነት ከፍተኛ ነው በመሆኑ የጋራ ግንዛቤ መያዝና በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ባንኮች በአንድ አገር ልማትና ብልጽግና ውስጥ የማይተካ ሚና አላቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው ግቦችና ዓላማዎች ለማሳካት ጉዳዩን በባለቤትነት እና በኃላፊነት ስሜት መምራትና መፈጸም ይጠበቅብናል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከተለያዩ ባንኮች በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙ የባንክ ፕሬዚዳንቶችና የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎች ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ከመከላከል እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻው ፖሊሲው የፈጠረውን ዕድል በመጠቀም አገራዊ ልማትን ለማረጋገጥ መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ውስጥ በግልጽ እንደተመለከታው የፋይናንስ ተቋማት ከወንጀሎቹ ጋር በተያያዘ አጠራጣሪ ግብይት ጋር ግንኙነት ያለው ተግባር ሲያጋጥማቸው ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በዚሁ መሰረት መደበኛ የአሰራርና ግንኙነት ስርዓት ተዘርግቶ ስራ እየተሰራ ነው።
IjIVGV
My name is Tizazu, and I have spent nearly a decade in various roles within the banking industry. Recently, I have observed a rise in intra-industry fraud, particularly those driven by technology. The availability of hacking tools, combined with increased technological awareness among some staff members, has made financial fraud more accessible. For example, the use of remote desktop tools by IT personnel has emerged as a prevalent method for committing fraud across the sector. I respectfully request that the institute (FIS) conducts research into these & related fraud cases within the banking industry to effectively mitigate potential threats. ✉ gebremariamsamsontizazu7@gmail.com