በዓለም አቀፍ ስታንደርዶች እና ሀገራዊ ማዕቀፎች ላይ ውይይት ተደረገ
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ/ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትንና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ብዜት በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን የመከላልና የመቆጣጠር ተግባራትን ለማጠናከር በዓለም አቀፍ ስታንደርዶች እና ሀገራዊ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ምክክር ተደረገ። የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ሀገራዊ የህግ ማዕቀፎችን መሠረት በማድረግ ወንጀሎቹን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ የሚገኝ በመሆኑ በእነዚህ የህግ ማዕቀፎች አተገባበር ቀጣይ ጉዳዮች ዙሪያ በተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች የአንድ ቀን ምክክር ተደርጓል።
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ፕሮግራሙን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የተዘጋጀው መድረክ ለተቋሙ ተልእኮ መሳካት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሰራተኛው እውቀት የሚጋራበት መሆኑን አውስተው ይህም ውስጣዊ ተቋማዊ አቅምን የማሳደግ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በውይይቱም ወቅት ወንጀሎቹን መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻል የተዘረጉ ዓለም አቀፍ ስታንደርዶችና ግዴታዎች፣ ሀገራዊ የህግ ማዕቀፎች፣ የውጤታማነት ግምገማ ስርዓቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተነስተው ተነስተው በስፋት ውይይት ተደርጎባቸዋል።
0 Comments