የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በቅርብ ጊዜ ስራ ለጀመሩ አዳዲስ ባንኮች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በህግ ሀላፊነት ከተጣለባቸው የፋይናንስ ነክ ተቋማት መካከል ባንኮች የሚገኙ በመሆናቸው ወንጀሉን ለመከላከል እንዲያስችላቸው እንዲሁም ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር ያለው የመረጃ መሳለጥ ለማጠናከር በቅርብ ጊዜ ስራ ለጀመሩ አዳዲስ ባንኮች ስለወንጀሎቹ አፈጻጸም እንዲሁም ባንኮች በምን አግባብ ወንጀሎቹን ለመከላከል በህግ የተጣለባቸውን ሀላፊነት ሊወጡ እንደሚችሉ ከጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የፋይናንስ ተቋማት በሚሰጡት አገልግሎት በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀሎች ጋር በተያያዘ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥም ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው ወንጀሎቹን ለመከላከል በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ላይ ተገልጧል፡፡ በመሆኑም ባንኮች በስራቸው ሂደት በተያያዘ አጠራጣሪ ግብይቶችን ሲመለከቱ ለአገልግሎቱ ሪፖርት ያደርጉበት የነበረው ሶፍትዌር ሌሎች አዳዲስ ጉዳዮች ተጨምረው የበለጸገ በመሆኑ ባንኮቹ ሶፍትዌሩን በመጠቀም አጠራጣሪ ጉዳዮችን ጨምሮ ሌሎች በህጉ የሚጠበቁባቸውን ሪፖርቶች በቀላሉ መላክ እንዲችሉ ግንዛቤ መፍጠርን ታሳቢ ሲሆን ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
1 Comments