የአገልግሎቱ የስድስት ወራት አፈጻጻም ተገመገመ
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሠራተኛ መድረክ ቀርቦ ተገመገመ። በዚህም አገልግሎቱ ባለፉት ስድስት ወራት በዋናነት ከሙስና፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት፣ ከህገ-ወጥ ሀዋላና ህገ-ወጥ የውጭ አገራት ገንዘብ ምንዛሪ፣ከታክስ ወንጀሎች፣ ከህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ወንጀሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ጉዳዮችን ለሚመለከታቸው አካላት በማስተላለፍ በሂደት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር ከአገልግለቱ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ ያደረጉት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ አገልግሎቱ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀሎች ጋር በተያየዘ አገልግሎቱ አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኃላፊነት ያለበት ተቋም በመሆኑ አዲስ በተዘረገው አደረጃጀት መሰረት የተቋሙን ውስጣዊ አሠራር በማጠናከር፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አቅም በማሳደግ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር ትኩረት እንደሚሰጥ አመላክተዋል።
0 Comments