የወንጀል ስጋትና ተጋላጭነት ጥናት ቡድኖች ተደራጁ
የወንጀል ስጋትና ተጋላጭነት ጥናት ቡድኖች ተደራጁ
------------------------------------------------------------
በወንጀል ተግባር የተገኘ ሃብት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ምንጭ ሊሆኑ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናት በማድረግ የመከላከልና መቆጠጠር እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ወርክሾፕ የተለያዩ የጥናት ቡድኖችን በማደራጀት ተጠናቀቀ።
ለሶስት ቀናት በተካሄደው በዚህ ወርክሾፕ በህግ የሰውነት መብት ከተሰጣቸው ድርጅቶችና አካላት፣ ከታክስ ወንጀሎች እንዲሁም ከቨርቹዋል ገንዘብና ቨርቹዋል ሃብቶች ጋር በተለያያዘ የሚፈፀሙና ሊፈፀሙ የሚችሉ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች እንዲሁም በወንጀል ተግባራቱ የተገኘው ሃብት ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብና የመጠቀም ወንጀሎች ስጋት፣ ተጋላጭነትና አገራዊ የጉዳት ደረጃ በጥናት ለመለየት በሚያስችሉ ስልቶችና ዘዴዎች ዙሪያ ሰፋ ያሉ ውይይቶች ተደርገዋል። በወርክሾፑ ማጠቃለያም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ተወካዮችንና በማካተት ሶስት የጥናት ቡድኖች ተደራጅተዋል።
0 Comments