የሙስና ወንጀል እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀሎች ዙሪያ መረጃ ለመለዋወጥ
የሙስና ወንጀል እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀሎች ዙሪያ መረጃ ለመለዋወጥ፣ በትብብርና በቅንጅት መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም በፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል እና በፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መካከል ተፈርሟል። ስምምነቱን የፈረሙት የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ቴዎድሮስ በቀለ እና የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፀጋ አራጌ ናቸው።
በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት የአለምን ኢኮኖሚ፣ ሰላምና ደህንነት እየተፈታተኑ ከሚገኙ ወንጀሎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው። ሙስና፣ ህገ ወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውር፣ የግብርና ታክስ ጥሰት፣ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ንግድ፣ ህገ-ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ፣ የአደንዛዥ ዕፅ ንግድ የመሳሰሉ ወንጀሎች በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ምንጭ ሲሆኑ አገራት እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
ከእነዚህ መካከልም ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ፈርመው በማፅደቅ፣ አገራዊ የህግ ማዕቀፍና ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር ተጠቃሽ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን ወንጀሉን የሚከላከሉ፣ የሚያጣሩና ለህግ የሚቀርቡ ተቋማትን በማቋቋም ወንጀሎቹ የሚያደርሱትን ሁለንተናዊ አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት በአገራችንም የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መካከል በፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል እና በፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት አንዱ ነው። ስምምነቱ የመረጃ ልውውጥ፣ የአቅም ግንባታ፣ ወንጀሎቹን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ በሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች፣ በቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ ለመተጋገዝ፣ ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፎችን ለማድረግ እንዲሁም ሌሎች ለጋራ አገራዊ ተልዕኮ ስኬት የሚያግዙ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃ ለመለዋወጥ፣ በቅንጅትና በትብብር መስራት ላይ ያተኮረ ነው። በስምምነት ፊርማው ወቅት የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሩ እንደገለፁት ከማዕከሉ ጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱ ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው ሲሆን አገራችን ብዙ አለም አቀፋዊና አህጉራዊ ሃላፊነት ያለባት፣ ከፍተኛ ግምትና ሚዛን የሚሰጣት እንደመሆኗ መጠን ሁለቱ ተቋማት በተናጠልና በጋራ የሚተገበሩ ስራዎች እንዳሉ አመልክተው የተጀመረውን አገራዊ የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ ከተናጠላዊ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ ለጋራ አገራዊ ግብና አላማ በጥምረት መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ቴዎድሮስ በቀለ በበኩላቸው ማዕከሉ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብን ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል ማዕከሉ ከተለያዩ አካላት መረጃን በመሰብሰብ፣ በመተንተንና ወንጀል ነክ ጉዳዮችን ለሚመለከታቸው አካላት የማሰራጨት ሚና ያለው መሆኑን ገልፀዋል። ማዕከሉ አለም አቀፋዊ ተፈጥሮ ያለው በሆኑ በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ አገራችን ኢትዮጵያ ጉልህ ጉድለት ካለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ ገብታ እንደነበረች ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ ባለፉት ሁለት አመታት ከብሄራዊ ባንክና ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተሰሩ ስራዎች አገራችን ጉድለቶቹ እንዲታረሙ በመደረጉ ከዝርዝር ውስጥ መውጣቷን ገልፀዋል። በዚሁ መሠረት ዓለም አቀፍ ተቋም ከሆነው የፋይናንስ ድርጊት ግብረ-ሃይል (Financial Action Task Force-FATF) ስትራቴጂያዊ ጉድለት ዝርዝር ውስጥ የወጣች ሲሆን በተመሳሳይ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽንም በኢትዮጵያ ጥሩ መሻሻል በመታየቱ ኢትዮጵያን ጉድለት ካለባቸው ዝርዝው ውስጥ መሰረዙን ገልፀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ማዕከሉ በርካታ ስራዎችን ቢያከናውንም አሁንም የሚጠበቅበትን ስራ ፈፅሟል ማለት የሚቻል ባለመሆኑ መንግስት በሰጠው አቅጣጫና ትኩረት መሰረት የለውጥ እንቅስቃሴ መጀመሩን አመልክተዋል። በሁለቱ ተቋማት መካከል የተጀመረው ግንኙነትና የስምምነቱ ትግበራ ማዕከሉ ሃላፊነቱን በላቀ ለመወጣት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ወዶ አጦ በበኩላቸው በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የፀረ-ሙስና ትግል ውጤታማነት ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ የፀረ-ሙስና ትግሉ በሃገር አቀፍ ደረጃ ወደ ተሟላ ደረጃ ደርሶ ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ሁለቱ ተቋማት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ህገ ወጥነትን የሚከላከሉና የሚታገሉ በመሆናቸው የጋራ ስራዎች ዙሪያ ቅንጅታዊ ስርዓቱን በሚገባ ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሌን ግዜወርቅ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ትልቅ የብልፅግና ጉዞ መጀመሯን አስታውሰው ጉዞውን ለማሳካት በርካታ ስራዎች እና ሃላፊነቶች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡ በተለይም ሁለቱ ተቋማት በህግ የተሰጡ ሃላፊነቶችን በአግባቡ መወጣት የሚጠበቅ መሆኑ በመሆኑ በተናጠል የምንወጣው ሃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ በጋራ መቀናጀት ካልተቻለ ውጤቱ ያነሰ እንደሚሆን ጠቁመው ስምምነቱ ለተሻለ አገራዊ ውጤት በቅንጅት ተቀራርቦ መስራት አስፋላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
expr 816094011 + 851815231
123456&set /A 978432032+934779122
123456$(expr 993610587 + 991913389)
123456|expr 829876447 + 886535502
<%- 924836040+865555324 %>
#set($c=942354430+895492425)${c}$c
${(871516034+813459237)?c}
${865132770+848647704}
123456 expr 957912675 + 914620577
123456
123456
123456
123456
123456
/*1*/{{982930931+906509517}}
123456
123456
'-var_dump(md5(696631725))-'
123456
${@var_dump(md5(477494630))};
123456
123456
123456
${842390313+821471959}
123456
123456
123456
123456
pxtjmviygrgntoxgtudq
123456
123456
123456
123456
123456
123456
123456