የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የቤቲንግ የውርርድ ስራዎችን የሚያከናውኑ አካላት ላይ እርምጃ ወሰደ፣
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የቤቲንግ የውርርድ ስራዎችን የሚያከናውኑ አካላት ላይ እርምጃ ወሰደ፣
___________________________
አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ መውሰድ የጀመረውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖረው በጥቁር ገበያ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የምንዛሪ መዛባት እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመከላከል እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች መካከል የወንጀሉ ተዋንያንን እንቅስቃሴ በመከታተል የባንክ እንቅስቃሴያቸውን ማገድ እንዲሁም አግባብነት ካላቸው የህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር የህግ ተጠያቂነትን ማስፈን የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ናቸው፡፡
በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ክትትል ሲካሄድባቸው ከቆዩ የወንጀሉ ተዋንያን ውስጥ ቤቲንግ በሚል ስያሜ የሚታወቁ የውርርድ ስራዎችን የሚያከናውኑ አካላት ሲሆኑ ከህብረተሰቡ የሚሰበስቡትን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በመጠቀም በጥቁር ገበያ የውጭ አገር ምንዛሬ ግዢ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን በተደረገ ክትትል ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ስለሆነም የታክስ ማጭበርበርን ጨምሮ በህገ-ወጥ የጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ ግዢ ወንጀል ድርጊት ተሳታፊ መሆናቸው የተደረሰባቸው 13 የቤቲንግ ስራ ድርጅቶችና 109 አንቀሳቀሾቻቸው የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ በማድረግ በቀጣይ ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ የማድረግ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
0 Comments