ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት በ44ኛው ቀጠናዊ ግምገማ እና 22ኛው የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ ተጠናቀቀ
ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር እና ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተውጣጡ አባላትን የያዘ የልዑካን ቡድን የተሳተፈበት በዛምቢያ ሊቪንግስቶን ከተማ ሲካሄድ የነበረው 44ኛው የምስራቃዊ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጸረ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ/ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ቡድን (Eastern and Southern Africa Anti-Money Laundering Group (ESAAMLG) የአባል ሀገራት ስብሰባ እና የ22ኛው የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እና ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡
በስብሰባው ላይም ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የፋይናንስ ደህንነት ዩነቶች ቡድን/ Egmont Group / አባል በመሆኗ አባል ለመሆን እየተንቀሳቀሱ ላሉ ሀገራት የኢትዮጵያ ልምድ ቀርቧል፡፡ በዚህም የአለም አቀፉ የፋይናንስ ደህንነት ዩኒቶችን ቡድን /Egmont Group/ለመቀላቀል በኢትዮጵያ በኩል የተከናወኑ ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም ችግሩን ለመፍታት የተሰሩ ስራዎች በኢትዮጵያ በኩል ቀርበዋል፡፡
የምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ የጸረ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ቡድን (Eastern and Southern Africa Anti-Money Laundering Group (ESAAMLG) የተባለው ተቋም የምሥራቅ እና የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራትን ያካተተ እና በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጊት ግብረ -ኃይል 40 ምክረ-ሀሳቦች እና በ11 የወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ውጤታማነት ምዘና መስፈርቶች መሰረት በአባል አገራቱ ላይ መደበኛ ክትትል በማድረግ በዓመት ሁለት ጊዜ በመደበኛነት ግምገማ ያደርጋል፡፡
0 Comments