ኢትዮጵያ በ44ኛው ቀጠናዊ ግምገማ ላይ እየተሳተፈች ነው
በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለ የተመራና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር እና ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ከአገልግሎት የተውጣጡ አባላትን የያዘ የልዑካን ቡድን በዛምቢያ ሊቪንግስቶን ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው 44ኛው የምስራቃዊ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጸረ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ/ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ቡድን ( Eastern and Southern Africa Anti-Money Laundering Group (ESAAMLG) የአባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ መደበኛ ስብሰባ ላይ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ እና ሽብርተኝነትንና ጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎችን ብዜት በገንዘብ መርዳት ወንጀሎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ አባል አገራት በወጣው ፕሮግራም መሰረት የሚገመገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም በይፋ ሪፖርት የሚወጣ ይሆናል፡፡
የምስራቃዊ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጸረ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ/ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ቡድን (ESAAMLG) የተባለው ይህ ቀጠናዊ ተቋም 19 አባል አገራትን እና 15 ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማትን በታዛቢነት የያዘ ነዉ።
ቀጠናዊ የግምገማ መድረኩ በዓለም የፋይናንስ ድርጊት ግብረ -ኃይል 40 ምክረ-ሀሳቦች እና በ11 የወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ውጤታማነት ምዘና መስፈርቶች ላይ የተመሰረተ ሲሆን የአገራትን መደበኛ የክትትል ሪፖርት መነሻ በማድረግ በዓመት ሁለት ጊዜ በመደበኛነት የሚካሄድ ነው፡፡
0 Comments