በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አስራር መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አስራር መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
ከሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለተወጣጡ የፖሊስ አባላት፣ አቃቢ ህጎች፣ ዳኞች፣ ከጸረ ሙስና ኮሚሽን ለተወጣጡ ባለሙያዎች እና የህዝብ ክንፍ አካላት በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀሎችን አስመልክቶ ለአራት ቀናት የቆየ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሀዋሳ ከተማ ተሰጠ፡፡
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀሎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ከሚያከናውናቸው በርካታ ተግባራት በተጨማሪ የባለድርሻ አካላት እና ህብረተሰቡ በወንጀሎቹ ዙርያ ያላቸውን ግንዛቤ በማሻሻል ቅንጅታዊ አሰራርን መፍጠር እንዲችል በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ሲሆን ከሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተለያዩ ተቋማት ለተወጣጡ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የዚህ ተግባር አንድ አካል ነው፡፡
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰላምን የጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ስልጠናውን ባስጀመሩበተ ወቅት እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ካስተናገደችው ሀገራዊ ለወጥ በኋላ ከሚስተዋሉ ወንጀሎች መካከል አንዱ በሀገር ወስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ አንዳንድ አካላት ህገወጥ በሆነ መልኩ ጤናማ ያልሆነ የፋይናንስ ስርዓት በሀገሪቱ እንዲፈጠር በማድረግ ኢኮኖሚ እንዳይረጋጋ እና የኑሮ ወድነት እንዲባባስ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በተያያዘም ከተለየዩ የወንጀል ተግባራት የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አሰመስሎ በማቅረብ ኢኮኖሚ እንዳይረጋጋ እንዲሁም የማህበረሰቡን ደህንነት ስጋት ላይ ለመጣል የሚደረጉ ጥረቶች በርካታ በመሆናቸው ይህንን ለመከላከል ከክልሉ የተለያዩ ተቋማት ለተወጣጡ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ግንዘቤ በመፍጠር ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከቱ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንደተቋሞቻቸው ስልጣንና ተግባር የተጠለባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል የክልሉ የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በመሆን የስልጠና ፕሮግራሙ እንዲዘጋጅ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
በወቅቱም በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀል ጽንሰ ሀሳብ፣ ታሪካዊ ዳራ፣ የሀገራዊ ስጋትና ተጋላጭነት፣ አለማአቀፋዊና ሀገርአቀፋ የህግ ማእቀፎች እና ወንጀሎቹን ለመከላከል መደረግ ስላለበት ሀገራዊ የቅንጅት ተግባራት እንደዚሁም ስለ ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ስልጠናንና ተግባር ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በመጡ ባለሙያዎች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎችም የተለያዩ ሀሳብ እና አስተያየቶቹን ያነሱ ሲሆን ስልጠናው ስለ በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ወንጀሎች በቂ ግንዛቤ እንደሰጣቸው በመጥቀስ እንደ የመጡበት ተቋም የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም እንደ ሀገር የወንጀሉን ተጋላጭነት ለመቀነስ በፌደራል ከሚደረገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ አደረጃጀት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ እና በፌደራልና በክልል ደረጃ ለሚገኙ የተለያዩ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ስለወንጀሎቹ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ በቅንጅት መስራት ላይ ተቋሙ ሊያተኩር እንደሚገባ እና ሌሎች አስተያየቶችን በማንሳት ውይይት ተደርጓል፡፡
0 Comments