ምክር ቤቱ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፀደቀ፡፡
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትን ማጠናከር በሀገሪቱ ከፋይናንስ እንቅስቃሴ እድገትና ከቴክኖሎጂ መዘመን ጋር እየተሳሰሩ የመጡትን የፋይናንስ ወንጀሎችን በተለይም በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እንዲሁም ሽብርተኝነትን እና የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ብዜት በገንዘብ መደገፍ ወንጀሎችን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል እንዲሆን፤ በተጨማሪም ሀገራችን ከተቀበለቻቸው እና ካጸደቀቻቸው ከዓለም አቀፍ የትብብር ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ ዓለም ዓቀፋዊና አህጉራዊ ትስስር በመፍጠር የወንጀል መንስኤዎችን፣ ስጋቶች እና ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል የህግ እና የአሰራር ክፍተቶችን መሙላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ተወያይቶ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
0 Comments