ተቋሙ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረገ
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ከኪሳቸው ገንዘብ በማዋጣት ታህሳስ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በወልድያ በመገኘት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 500 ሺህ ግምት ያለው የበጎች፣ የፍየል እና የውሃ ድጋፍ በማድረግ ለሠራዊቱ ድጋፍና አጋርነቱን ገልጿል።
በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለ ይዘን የመጣነው ትልቅ ነገር ነው ለማለት ሳይሆን በተመዘገባው ከፍተኛ ድል የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ ለመግለፅ መሆኑን ገልፃው ለሠራዊቱ የተደረገው ይህ ድጋፍ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በየወሩ ለመከላከያ ሰራዊት ከሚያደርጉት ድጋፍ በተጨማሪ ከራሳቸው ከኪሳቸው ገንዘብ በማዋጣት የደስታችን መግለጫ አካል እንዲሆን ድጋፉን ይዘን መጥተናል ብለዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለ ከስንቅ ድጋፍ በተጨማሪ ተቋሙ ግንባር ድረስ በማሳተፍ፣ ለሽብርተኞች የገንዘብ ድጋፍ እንዳይደረግ ክትትል በማድረግና በማገድ የድርሻውን በመወጣት ላይ መሆኑን አብራርተዋል። የህዝቡ ደስታ የእኛም ደስታ በመሆኑ በቦታው በመገኘት ደስታችንን መግለጽ በመቻላችን ደስታ ተሰምቶናል ያሉት አቶ ቴዎድሮስ በቀጣይም ለሀገር መሰዋፅት እየከፈለና ህይወቱን እየሰጠን ላለው መከላከያ ጊዜያችንን በመስጠት ሃላፊነታችንን በመወጣት፣ የዘማች ቤተሰቦችን በመደገፍ እና በሌሎችም ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም ለሠዊራቱ ያለንን ክብር እንገፃልን ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ሠራዊቱን በመወከል የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት ኮሎኔል ከማል ኤቢሶ በበኩላቸው ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሀገር መከላከያ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀው አሁንም በርካታ መንግስታዊ ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሠራዊቱ ጎን መሆናቸውን እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትም በግንባር መሳተፍን ጨምሮ የተደረገው ድጋፍ ሠራዊነቱ ቀጣይ ግዳጁን በብቃት እንዲያጠናቅቅ የሚያግዝ ነው ብለዋል። አክለውም የደህንነት ተቋማትም የጠላትን እንቅስቃሴ በመከታተል ለሰራዊቱ በቂ መረጃ በማቅረብ ሠራዊቱ ከፍተኛ ድል እንዲቀዳጅ አድርገዋል ብለዋል። በተቋሙ አመራሮችና ለሰራዊቱ የተደረገው ድጋፍ ሰራዊቱ በቀጣይም ለሀገራችን መሰዋዕት በመክፈል ተጨማሪ ድሎችን ለማስመስገብ አጋዥ መሆኑን ጠቅሰው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
0 Comments